እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤
ኤርምያስ 51:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎን ለዓለም ሕዝብ እልቂት ምክንያት ሆናለች፤ ለብዙ እስራኤላውያን እልቂት ምክንያት በመሆንዋም እነሆ ባቢሎን ራስዋ መውደቅ አለባት፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በምድር ሁሉ የታረዱት፣ በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባቢሎን በምድሪቱ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ወድቀዋል እንዲሁ ለእስራኤል ተወግተው ለሞቱት ባቢሎን መውደቅ አለባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቢሎንም በእስራኤል ስለ ተገደሉት ትወድቃለች፤ ስለ ባቢሎንም በምድር ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፥ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤
ስለዚህ የጽዮን ከተማ ሕዝብ “በእኛ ላይ የደረሰው ሥቃይ በባቢሎን ላይ ይድረስ!” ይላሉ፤ የኢየሩሳሌምም ሕዝብ “የእኛ ደም እንደ ፈሰሰ የባቢሎናውያንም ደም ይፍሰስ!” ይላሉ።
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።