ኤርምያስ 51:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠላት ሠራዊት የወንዙን መሸጋገሪያ ይዞ የዘብ መጠበቂያዎቹን አቃጠለ፤ የባቢሎን ወታደሮች በመሸበር ተርበደበዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካዎቿ እንደ ተያዙ፣ የወንዝ ዳር ምሽጎቿ እንደ ተቃጠሉ፣ ወታደሮቿም እንደ ተደናገጡ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዙም መሻገርያዎች ተይዘዋል፥ የውኃ ማቆርያዎቹም በእሳት ተቃጥለዋል ወታደሮቹም በሽብር ውስጥ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሻገሪያዎችዋም ተይዘዋልና፥ ቅጥርዋም በእሳት ተቃጥሎአልና፥ ሰልፈኞችም ተማርከዋልና።” |
የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።
የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።
ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ከበው ሳለ ወታደሮቹ በሌሊት አምልጠው ነበር፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ በሚወስደው መንገድ በኩል በማለፍ ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው በቅጽር በር ወጥተው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፤