የእነርሱ ዕቅድ ግን ይህ አይደለም፤ ይህም ጉዳይ በሐሳባቸው ውስጥ የለም፤ የእነርሱ ዓላማ ግን ጥቂቶቹን ሳይሆን ብዙዎችን ሕዝቦች ለማጥፋት ነው።
ኤርምያስ 49:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐጾር ነዋሪዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ ስለ መከረባችሁና ክፉ ዕቅድ ስላቀደባችሁ ርቃችሁ ሽሹ፤ በጥልቁም ዋሻ ተደበቁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣ በጥድፊያ ሽሹ፤ በጥልቅ ጕድጓድ ተሸሸጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ ጠንክሯልና፣ ወረራም ዶልቶባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በአሦር የምትኖሩ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ አሳብም አስቦባችኋልና ሽሹ ወደ ሩቅም ስፍራ ሂዱ በጥልቁም ውስጥ ተቀመጡ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በአሦር የምትኖሩ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ ክፉ አሳብንም አስቦባችኋልና ሽሹ፤ ወደ ሩቅም ሂዱ፤ በጥልቅ ጕድጓድም ውስጥ ተቀመጡ፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ አሳብም አስቦባችኋልና ሽሹ ወደ ሩቅም ሂዱ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የእነርሱ ዕቅድ ግን ይህ አይደለም፤ ይህም ጉዳይ በሐሳባቸው ውስጥ የለም፤ የእነርሱ ዓላማ ግን ጥቂቶቹን ሳይሆን ብዙዎችን ሕዝቦች ለማጥፋት ነው።
‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እነዚህ ሕዝቦች ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ በሆነው በአገልጋዬ በናቡከደነፆር ሥልጣን ሥር እንዲገዙለት ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ የምድር አራዊትም ሳይቀሩ ይገዙለታል።