ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
ኤርምያስ 48:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሉሒት ሲወጡ ምርር ብለው እያለቀሱ ይወጣሉ፤ ወደ ሖሮናይም ቊልቊለት ሲወርዱ በውድመቱ ምክንያት የጭንቀት ድምፅ ያሰማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉኛ እያለቀሱ፣ ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ ወደ ሖሮናይም ቍልቍል ይወርዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሉሒት አቀበት መራር ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቁልቁለት የጥፋትንና የጣርን ጩኸት ሰምተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሎዊት ዓቀበት ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም መንገድ የመባባትን ጩኸት ሰምተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሉሒት ዓቀበት ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቍልቍለት የጥፋትንና የመባባትን ጩኸት ሰምተዋል። |
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።