እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፤ ቤንሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ በመቀመጥ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፤
ኤርምያስ 41:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስማኤልና ስምንት ሰዎቹ ግን ከዮሐናን እጅ አምልጠው ወደ ዐሞን ምድር ኰበለሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ዐብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋራ ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ፥ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። |
እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፤ ቤንሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ በመቀመጥ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፤
ነገር ግን በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዘር የነበረውና የኤሊሻማዕ የልጅ ልጅ የሆነው የነታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ሄደ፤ በዚያም አደጋ ጥሎ ገዳልያን ገደለው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተገኙትን እስራኤላውያንንና ባቢሎናውያንን ሁሉ ገደለ፤
የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ።
በምሽት ጊዜ ዳዊት በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ እስከ ማግስቱ ማታ ድረስ ተዋጋቸው፤ በግመል ላይ ተቀምጠው እየጋለቡ ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር ከነዚያ ወራሪዎች ያመለጠ አንድም አልነበረም፤