ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።
ኤርምያስ 39:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ በሌሊት ከከተማይቱ ወጥተው ለማምለጥ ሞከሩ፤ በቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ በኩል አድርገው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው መውጫ በር አቋርጠው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ አመለጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ እነርሱን ባዩ ጊዜ ሸሹ፤ በሌሊት በንጉሡ አትክልት ስፍራ በኩል አድርገው በሁለቱ ቅጥር መካከል ከከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ዓረባም አመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወታደሮቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በነበረው በር በኩል ከከተማይቱ ወጡ፤ መንገዳቸውንም ወደ ዓረባ አድርገው ተጓዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ሰልፈኞቹም ሁሉ በአዩአቸው ጊዜ፥ በሌሊት ሸሹ፤ በንጉሡም አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል በነበረው ደጅ ከከተማዪቱ ወጡ፤ በዓረባም መንገድ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰልፈኞቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ፥ በዓረባም መንገድ ወጡ። |
ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።
ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።
ከዚያ በኋላ ግን እኔ እግዚአብሔር “የእግዚአብሔር መሠዊያ” ተብላ የምትጠራውን የእስራኤል ከተማ አስጨንቃለሁ፤ እዚያም ሐዘንና የለቅሶ ዋይታ ይሆናል፤ ከተማይቱም በደም እንደ ተሸፈነ መሠዊያ ትሆናለች።
ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳል፤ እኔ በሞት እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፤ ከባቢሎናውያን ጋር ለመዋጋት ቢሞክር እንኳ አይሳካለትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እነርሱን የሚያስተዳድረው መስፍን ዕቃውን ጠቅልሎ በትከሻው በመሸከም እነርሱ ግድግዳ ነድለው በሚያወጡለት ቀዳዳ ሾልኮ በጨለማ ይሰደዳል፤ ዐይኑንም ስለሚሸፍን ምድሪቱን አያይም።
“ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤