በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
ኤርምያስ 38:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ጊዜ ድረስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ቈየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ ኤርምያስ በዘበኞች አደባባይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ በግዞት ቤቱ አደባባይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ። |
በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! እንድታዳምጠኝና የምጠይቅህን እንድትፈጽምልኝ እለምንሃለሁ፤ ይኸውም እስር ቤት ወደ ሆነው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ፤ ወደዚያ ከመለስከኝ በእርግጥ እሞታለሁ።”
ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ እንዲዘጋብኝ አዘዘ፤ እኔም በዚያ ቈየሁ፤ ዳቦ ከከተማይቱ ጨርሶ እስከ ጠፋም ድረስ ከዳቦ መጋገሪያዎች አንድ ዳቦ በየቀኑ ይሰጠኝ ነበር።
ከዚያም በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ መጥተው ጠየቁኝ፤ እኔም ልክ ንጉሡ ያለኝን ብቻ ነገርኳቸው፤ እኔና ንጉሡ ስንወያይ የሰማ ማንም ስላልነበረ ከዚያ በኋላ ጥያቄአቸውንም አቆሙ፤
ታስሬበት ከነበረው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ከሚገኘው ዘብ ጠባቂዎች ክፍል እንድወጣ አስደረገ፤ እኔም የሳፋን የልጅ ልጅ በሆነው በአሒቃም ልጅ በገዳልያ እጅ ወደ ቤቴ ተወሰድኩ፤ እኔም ከሕዝቤ ጋር በዚያ ኖርኩ።
እንዲሁም ስደቴንና መከራዬን ታውቃለህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና በትዕግሥት የተቀበልኩትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ።