ኤርምያስ 36:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ሆነ መኳንንቱ ይህን ሁሉ ከሰሙ በኋላ ምንም ዐይነት ፍርሀት አልተሰማቸውም ወይም በሐዘን ልብሳቸውን አልቀደዱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ሆነ ይህን ሁሉ ቃል የሰሙት መኳንንት ሁሉ አንዳች አልፈሩም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሆነ እነዚህን ቃላት ሁሉ የሰሙ ባርያዎቹ በጠቅላላ አልፈሩም ልብሳቸውንም አልቀደዱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ ይህንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገልጋዮቹ ሁሉ አልደነገጡም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ይህንም ቃል ሁሉ የሰሙ ባሪያዎቹ ሁሉ አልፈሩም ልብሳቸውንም አልቀደዱም። |
ኤልያስ ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ አክዓብ ልብሱን በመቅደድና አውልቆ በመጣል ማቅ ለበሰ፤ እህል መቅመስንም እምቢ አለ፤ ማቁንም እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ ፊቱ ጠቊሮ ይታይ ነበር።
ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤ ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ።
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
ከዚህ በኋላ የቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የሕልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊው ሼብናና የታሪክ መዝጋቢ የነበረውም የአሳፍ ልጅ ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስም ቀርበው የአሦርያውያን ባለሥልጣን የተናገረውን ሁሉ አስረዱ።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋልና። አሁን ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።