ኤርምያስ 35:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እኔ ኤርምያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ለሬካባውያን ወገን የተናገረውን ቃል እንዲህ ብዬ ገለጥኩላቸው፦ “የቀድሞ አባታችሁ ኢዮናዳብ የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽማችኋል፤ ትምህርቱንም ሁሉ ተከትላችኋል፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ አድርጋችኋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስለ ጠበቃችሁ፤ መመሪያውን ስለ ተከተላችሁ፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ ስለ ፈጸማችሁ’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ለሬካባውያን ቤት እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ ትእዛዝ ታዝዛችኋልና፥ ትእዛዛቱንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፥ ያዘዛችሁንም በሙሉ ፈጽማችኋልና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ሰምታችኋልና፥ ትእዛዙንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፥ ያዘዛችሁንም ሁሉ አድርጋችኋልና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ ትእዛዝ ታዝዛችኋልና፥ ትእዛዙንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፥ ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋልና፥ |
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”
“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።