እነርሱ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ፦ “እኛ የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ የሬካብ ልጅ የነበረው አባታችን ኢዮናዳብ እኛም ሆንን ዘሮቻችን ሁሉ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ እንዳንጠጣ አዞናል።
ኤርምያስ 35:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንኳን ኖረናል፤ የቀድሞ አባታችን ኢዮናዳብ ላዘዘን ቃል ሁሉ በሙሉ ልብ ታዛዦች ሆነናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንኳን ኖረናል፤ አባታችን ኢዮናዳብ ያዘዘንንም ሁሉ ጠብቀናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጠናል፥ እኛም በመታዘዝ አባታችን ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንኳን ውስጥ ተቀምጠናል፤ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ ሰምተናል፤ አድርገናልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በድንኳንም ውስጥ ተቀምጠናል፥ ታዝዘናል፥ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል። |
እነርሱ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ፦ “እኛ የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ የሬካብ ልጅ የነበረው አባታችን ኢዮናዳብ እኛም ሆንን ዘሮቻችን ሁሉ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ እንዳንጠጣ አዞናል።
እንዲሁም መኖሪያ ቤት መሥራት፥ እርሻ ማረስ፥ የወይን ተክል ቦታዎችን ይዘን መንከባከብ እንደማይገባን ነግሮናል፤ እንደ እንግዶች በዚህች ምድር ለብዙ ጊዜ መቀመጥ እንችል ዘንድ በድንኳን መኖር እንደሚገባን አዞናል።