ኤርምያስ 33:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና ከሌዊ ወገን የሆኑትን ካህናት ቊጥር አበዛለሁ፤ ብዛታቸውም ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋና እንደ ሰማይ ከዋክብት ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እንዲሁም በፊቴ የሚቆሙትን ሌዋውያን እንደማይቈጠሩ እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደማይሰፈር የባሕር አሸዋ አበዛቸዋለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይን ሠራዊት መቁጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባርያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይን ሠራዊት መቍጠር፥ የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይን ሠራዊት መቍጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ። |
ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።
በዚያም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፤ በደስታም እልል ይላሉ፤ አበዛቸዋለሁ እንጂ ቊጥራቸው አይቀንስም፤ ክብር እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አይናቁም።
እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በሠሩት በደል ምክንያት ይጥላቸዋል ማለት የሚቻለው የሰማይ ስፋቱ ተለክቶ፥ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተመርምረው ለመታወቅ ቢችሉ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
እኔም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርሁ፤ በእነርሱ ሁሉ ውስጥ እስትንፋስ ገባባቸው፤ ሁሉም ሕይወት አግኝተው ቆሙ፤ እጅግ ብዙ ሠራዊትም ሆኑ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ እኔን ከድተው ከፊቴ ሲርቁ፥ በቤተ መቅደስ በታማኝነት ጸንተው እኔን ሲያገለግሉ የኖሩና ነገዳቸው ከሌዊ ወገን ሆኖ ከሳዶቅ የተወለዱ ካህናት አሉ፤ ስለዚህም ስብና የመሥዋዕት ደም በማቅረብ በፊቴ ቆመው ሊያገለግሉኝ የሚገባቸው እነርሱ ናቸው፤
የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤
በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደ ጋሻ መከታ እሆንላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ እጅግ ደካማ የተባለው እንኳ የዳዊትን ያኽል ብርቱ ይሆናል፤ የዳዊት ልጆች እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ወይም እንደ መላእክት ሆነው ሕዝቡን ይመራሉ።
የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።