ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እኛ ታላቅ በደል ሠርተናል፤ ከኃጢአታችንም ብዛት የተነሣ እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናታችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀናል፤ ስለዚህም ለሰይፍ ተዳረግን፤ ሀብታችንንም ተዘረፍን፤ በመታሰር ተማርከን ተወሰድን፤ እነሆ፥ አሁንም እንዳለንበት ሁኔታ እስከ መጨረሻ ተዋርደናል።
ኤርምያስ 32:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፣ እነርሱ፣ ነገሥታታቸው፣ ባለሥልጣኖቻቸው፣ ካህናታቸው፣ ነቢያታቸው፣ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ባደረጉት ክፋት ሁሉ አስቈጡኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም የማደርገው እኔን ለማስቈጣት፥ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፥ አለቆቻቸውና ካህናቶቻቸው፥ ነብዮቻቸውና የይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፥ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፥ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም፥ የይሁዳም ሰዎች፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ስለ አደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፥ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው አለቆቻቸውም ካህናቶቻቸውም ነቢያቶቻቸውም የይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፥ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው። |
ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እኛ ታላቅ በደል ሠርተናል፤ ከኃጢአታችንም ብዛት የተነሣ እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናታችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀናል፤ ስለዚህም ለሰይፍ ተዳረግን፤ ሀብታችንንም ተዘረፍን፤ በመታሰር ተማርከን ተወሰድን፤ እነሆ፥ አሁንም እንዳለንበት ሁኔታ እስከ መጨረሻ ተዋርደናል።
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሌባ በሚያዝበት ጊዜ እንደሚያፍር፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝብ ነገሥታትና መኳንንት፥ ካህናትና ነቢያት ሁሉ የምታፍሩበት ጊዜ ይመጣል።
እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።
“እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን?
ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል።
ጌታ ሆይ! አንተ እውነተኛ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን፥ እኛ በምድር ሁሉ ላይ የበተንከን በቅርብና በሩቅ ያለን የይሁዳ ሕዝብ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና መላዋ የእስራኤል ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ኀፍረት ደርሶብናል።