“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
ኤርምያስ 31:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንተ ርቀን ብንሄድም እንኳ አሁን ንስሓ ገብተናል፤ በዕፍረትና በጸጸት ራሳችንን ዝቅ አድርገን ደረታችንን እንመታለን፤ በወጣትነት ዘመናችን ለፈጸምነው ኃጢአት ራሳችንን እንወቅሳለን።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንተ ከራቅሁ በኋላ፣ ተመልሼ ተጸጸትሁ፤ ባስተዋልሁም ጊዜ፣ ጭኔን መታሁ፤ የወጣትነት ውርደቴን ተሸክሜአለሁና ዐፈርሁ፤ ቀለልሁም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ በኀዘን ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ ተዋረድሁም።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፤ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፥ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም ብሎ ሲያለቅስ ሰማሁ። |
“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
ኀፍረትም ሆነ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ በወጣትነትሽ ጊዜ የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺአለሽ፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ብቸኛ ሆነሽ ያሳለፍሽውን የስድብ ዘመን አታስታውሺም።
በብልጽግና በምትኖሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ተናገራችሁ፤ እናንተ ግን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምታደርጉት ይህንኑ ነው። እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ አላችሁ።
እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከክፉ አድራጎት በስተቀር ምንም ያደረጉት መልካም ነገር የለም። በተለየም የእስራኤል ሕዝብ በእጃቸው በሠሩት ጣዖት እኔን ከማስቈጣት በቀር ምንም የሠሩት ነገር የለም።
የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤ ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው። እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤ ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።
አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ።
መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
ከሞት ያመለጣችሁት እናንተ ተማርካችሁ በሄዳችሁበት ሕዝቦች መካከል ታስታውሱኛላችሁ፤ የምታስታውሱኝም ከእኔ በራቀው ሥርዓተ አልባ በሆነው ክፉ ልባችሁና ሥርዓተ አልባ በሆነው ዐይናችሁ ጣዖቶችን በመመልከት ስላሳዘናችሁኝ ነው። በርኩስ ድርጊቶቻችሁም ላደረጋችሁት ክፉ ነገር ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
“ቀራጩ ግን በሩቅ ቆመና፥ ቀና ብሎ ወደ ሰማይ ለማየት እንኳ አልደፈረም፤ ነገር ግን በእጁ ደረቱን እየመታ፥ ‘አምላክ ሆይ! እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ!’ ይል ነበር።
እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል።