ኤርምያስ 30:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ፈንታ ለእኔ ለአምላካቸው ይሰግዱልኛል፤ እኔ በዙፋን ላይ ለማስቀምጥላቸው የዳዊት ዘር ለሆነውም ንጉሣቸው ይገዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣ ለዳዊት ይገዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌታ አምላካቸውንና የማስነሣላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም፥ ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዳዊት ዘር መካከል ጻድቅ የሆነውን ለንጉሥነት የምመርጥበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ንጉሥ በጥበብ ያስተዳድራል፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ትክክልና ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል።
ስለ እናንተ ያለኝን ዕቅድ የማውቅ እኔ ነኝ፤ ይህም ዕቅድ ክፋትን ሳይሆን ሰላምን በማስገኘት እናንተ በተስፋ የምትጠብቁት መልካም ነገር የሚፈጸምበት ነው፤
የራሳቸው ወገን ከመካከላቸው ተነሥቶ መሪአቸው ይሆናል፤ እኔ ራሴ ስለማመጣው እርሱ ወደ እኔ ይቀርባል፤ አለበለዚያማ ማን ደፍሮ ሊቀርብ ይችላል?
በዚያን ጊዜ የዳዊት ዘር ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ጻድቅ ንጉሥ እመርጣለሁ፤ ያም ንጉሥ በአገሪቱ ላይ ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል፤ ትክክለኛ ፍርድም ይሰጣል።
ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።
መበስበስ እንዳይደርስበት እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣው ለማስረዳት፥ ‘ቅዱሱን የታመነ በረከትን ለዳዊት የተሰጠውን ተስፋ እሰጣችኋለሁ’ ብሎ ተናግሮአል።
ነገር ግን ዳዊት ይህን የተናገረው ነቢይ ስለ ነበረና እግዚአብሔር ‘ከዘርህ አንዱን በዙፋንህ ላይ አስቀምጥልሃለሁ’ ሲል በመሐላ የሰጠውን የተስፋ ቃል ያውቅ ስለ ነበር ነው፤