ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እኛ ታላቅ በደል ሠርተናል፤ ከኃጢአታችንም ብዛት የተነሣ እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናታችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀናል፤ ስለዚህም ለሰይፍ ተዳረግን፤ ሀብታችንንም ተዘረፍን፤ በመታሰር ተማርከን ተወሰድን፤ እነሆ፥ አሁንም እንዳለንበት ሁኔታ እስከ መጨረሻ ተዋርደናል።
ኤርምያስ 2:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሌባ በሚያዝበት ጊዜ እንደሚያፍር፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝብ ነገሥታትና መኳንንት፥ ካህናትና ነቢያት ሁሉ የምታፍሩበት ጊዜ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣ የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣ ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር እንዲሁ የእስራኤል ቤት፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም አለቆቻቸውም ካህናቶቻቸውም ነብዮቻቸውም ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፤ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር እንዲሁ የእስራኤል ቤት፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም አለቆቻቸውም ካህናቶቻቸውም ነቢያቶቻቸውም ያፍራሉ። |
ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እኛ ታላቅ በደል ሠርተናል፤ ከኃጢአታችንም ብዛት የተነሣ እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናታችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀናል፤ ስለዚህም ለሰይፍ ተዳረግን፤ ሀብታችንንም ተዘረፍን፤ በመታሰር ተማርከን ተወሰድን፤ እነሆ፥ አሁንም እንዳለንበት ሁኔታ እስከ መጨረሻ ተዋርደናል።
እነርሱንም የሚያመልኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ ጣዖትን የሚሠሩ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሁሉም ይሰብሰቡና በፊቴ ይቁሙ፤ ሁሉም በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ያፍራሉም።
ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።
በምትሠሩት ኃጢአት ምክንያት ነፋስ ገለባን ጠራርጎ እንደሚወስድ፥ መሪዎቻችሁ ተጠራርገው ይወሰዳሉ። የተማመናችሁባቸው የጦር ጓደኞቻችሁም ተማርከው ወደ ባዕድ ሀገር ይወሰዳሉ፤ ኀፍረትና ውርደትም ይደርስባችኋል።
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል።
ሞአብ ሆይ! እስራኤል ከሌቦች ጋር የተያዘች ባትሆንም እንኳ አንቺ እርስዋን መሳለቂያ አድርገሽ ስለ እርስዋ በተናገርሽ ቊጥር ራስሽን ትነቀንቂ ነበር።
አንቺም ውርደትሽን ተከናንበሽ ባደረግሽው ነገር ሁሉ ታፍሪአለሽ። ሰዶምና ሰማርያ ይህን ሁናቴሽን በሚያዩበት ጊዜ ያንቺን ያኽል ኃጢአተኞች ባለመሆናቸው ይጽናናሉ።
ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘ይህን ርግማን እልካለሁ፤ ወደ እያንዳንዱ ሌባና በስሜ ምሎ በሐሰት ወደሚናገር ሰው ቤት ይገባል፤ በገባበትም ጊዜ በዚያ ቈይቶ ቤታቸውን ሁሉ ያፈራርሰዋል’ ይላል።”