እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት።
ኤርምያስ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመረጥኳቸው ሕዝቤ በሁሉ አቅጣጫ በጭልፊቶች እንደ ተከበበች ወፍ ሆነዋል፤ ስለዚህ ሌሎችም የዱር አራዊት መጥተው ሥጋቸውን በመብላት እንዲደሰቱ ጥሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት፣ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን? ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤ እንዲቀራመቷትም አምጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ እንዲበሉም አምጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስቴ እንደ ጅብ ጕድጓድ ናትን? ወይስ በዙሪያዋ የሚከቡአት የሽፍቶች ዋሻ ናትን? የምድር አራዊት ሁሉ ይበሉአት ዘንድ ተሰብስበው ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው። |
እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት።
እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤
“ጽዮን እጆችዋን ትዘረጋለች፤ ነገር ግን ማንም የሚያጽናናት የለም፤ ጐረቤቶቹ ሁሉ የያዕቆብ ዘር ጠላቶች እንዲሆኑ እግዚአብሔር አዟል። ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥር ቀንዶች አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ወደ ጥፋት ያደርሱአታል፤ ራቁትዋን ያስቀሩአታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤