በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በማጓደል ዐምፀናል፤ አምላካችንን ትተን ወደ ኋላ አፈግፍገናል፤ በልባችን ውስጥ ውሸትን አውጠንጥነን ስም በማጥፋትና በከሐዲነት ገልጠናቸዋል።
ኤርምያስ 12:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ በእኔ ላይ ተነሥተው እንደ ዱር አንበሳ ያገሡብኛል፤ ይህንንም አድራጎታቸውን እጠላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳ ተነሥታብኛለች፤ በእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ ስለዚህ ጠላኋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን በእኔ ላይ አንሥታለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስቴ በዱር እንደ አለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋንም አንሥታብኛለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፥ ድምፅዋን አንሥታብኛለች፥ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። |
በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በማጓደል ዐምፀናል፤ አምላካችንን ትተን ወደ ኋላ አፈግፍገናል፤ በልባችን ውስጥ ውሸትን አውጠንጥነን ስም በማጥፋትና በከሐዲነት ገልጠናቸዋል።
እርቃንዋን ወደ አደባባይ በመውጣት አመንዝራነትዋ በሰው ሁሉ ዘንድ እንዲጋለጥ አደረገች፤ እኔም እኅትዋን የተጸየፍኩትን ያኽል እርስዋንም ተጸየፍኳት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በጌልገላ ሳሉ ክፉ ሥራቸው ተገለጠ፤ እኔም በዚያ የእነርሱን ሥራ መጥላት ጀመርኩ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ ከሰጠኋቸው ምድር አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለእነርሱ ፍቅር አላሳያቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ሆነዋል።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፦ “በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኋል፤ ከጦርነት ተመልሰው በመተማመን በመካከላችሁ የሚያልፉትን ሰላማዊ ሰዎች ገፈፋችሁ፤