ኤርምያስ 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ገና ልጅ ስለ ሆንኩ እንዴት እንደምናገር አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ “ወዮ! ጌታ አምላኬ፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እንዴት እንደምናገር አላውቅም” አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “ወዮልኝ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እናገር ዘንድ አልችልም” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ። |
ነገር ግን ሙሴ “ወገኖቼ እስራኤላውያን እንኳ አልሰሙኝም፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል? እንደምታየኝ እኔ ኰልታፋ ነኝ” ሲል መለሰ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ነቢያቱ ‘ጦርነት ሆነ ራብ አይኖርም’ እያሉ ለሕዝቡ ይናገራሉ፤ ‘በምድራችን ዘላቂ ሰላም ብቻ እንደሚሰፍን እግዚአብሔር ተናግሮአል’ ይላሉ።”
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።