የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።
ያዕቆብ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፥ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ፥ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል። |
የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
“እናንተ የጽዮን ሕዝብ ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ እርሱ በትክክል ፈርዶ እንደ ወትሮው በበጋና በክረምት ወራት በቂ ዝናብ ሰጥቶአችኋል።
እግዚአብሔር በበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ለምኑት፤ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ እግዚአብሔር ነው፤ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም የሚሰጥ እርሱ ነው።
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
በዚህ ምክንያት በወንድሞች መካከል፥ “ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም” የሚል ወሬ ተሰራጨ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፥ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲኖር ብፈቅድ አንተ ምን አገባህ” አለ እንጂ፥ “አይሞትም” አላለም።
ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር የክረምቱንና የበልጉን ዝናብ በወቅቱ ለምድራችሁ ይልካል፤ በዚህም ዐይነት ለእናንተ ሲሳይ የሚሆነው እህል፥ ወይን ጠጅና የወይራ ዘይት፥
በአምላካችንና በአባታችን ፊት እምነታችሁ የሚሠራውን፥ ለፍቅር የምታደርጉትንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ በትዕግሥት መጠባበቃችሁን ሳናቋርጥ እናስታውሳለን።
በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ፤ ሰውን የሚያማ ወይም በሰው ላይ የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል፤ በሕግ ላይ ብትፈርድ ደግሞ ፈራጅ መሆንህ ነው እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም።
ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ብዙ ሀብት አከማችታችኋል።
እነርሱ “ጌታ ኢየሱስ ይመጣል ተብሎ ተስፋ ተሰጥቶ አልነበረምን? ታዲያ፥ የት አለ? የቀድሞ አባቶቻችን ከሞቱበት ጊዜ አንሥቶ ሁሉ ነገር ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እንደ ነበረው ነው” ይላሉ።