ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ፦ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ይህን በደል ያመጣህብን ምን ያስቀየምኩህ ነገር ቢኖር ነው? አንተ ያደረግህብኝን ነገር ከቶ ማንም ሰው አያደርገውም፤
ያዕቆብ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንድ አፍ ምስጋናና ርግማን ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህ ሊሆን አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ! ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። |
ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ፦ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ይህን በደል ያመጣህብን ምን ያስቀየምኩህ ነገር ቢኖር ነው? አንተ ያደረግህብኝን ነገር ከቶ ማንም ሰው አያደርገውም፤
እርስዋም “አይሆንም ወንድሜ ሆይ! እባክህ አታዋርደኝ! የዚህ ዐይነቱ አሳፋሪ ተግባር በእስራኤል ተፈጽሞ አያውቅም! ስለዚህ ይህን ትልቅ ብልግና አትፈጽም፤
የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።
እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን?
ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።