ኢሳይያስ 64:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ እንዲገለጥ፥ አሕዛብም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አደሮ ማር በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ጠላቶችህን እሳት ትበላቸዋለች፤ ስምህም በእነርሱ ላይ ይታወቃል፤ አሕዛብም በፊትህ ይደነግጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አህዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ። |
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
እግዚአብሔር በጰራጺም ተራራ ላይና በገባዖን ሸለቆ ላይ እንዳደረገው፥ አሁንም ያልተለመደ ሥራውን ለመሥራትና ለሰው እንግዳ የሆነው ተግባሩን ለመፈጸም ይነሣል።
ለኢየሩሳሌም የማደርጋቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ በሚሰሙት ሕዝቦች ፊት ለእኔ ገናናነት፥ ክብርና ምስጋናን ታስገኛለች፤ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ የማደርገውን መልካም ነገሮችና ለከተማይቱ የማመጣላትን ሀብትና በጎነት በሚሰሙበት ጊዜ አሕዛብ ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔም እንደዚሁ አደርግባችኋለሁ፤ ስለዚህ ይህን ስለማደርግባችሁ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር በፍርድ ለመገናኘት ተዘጋጁ!”
በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማል፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በሰፊ ሸለቆ በሁለት ይከፈላል፤ ስለዚህም የተራራው እኩሌታ ወደ ሰሜን እኩሌታውም ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል።