ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኢሳይያስ 61:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር ቡቃያዎችን እንደምታበቅል፥ የአትክልት ቦታም ተክሎችን እንደምታሳድግ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ጽድቅና ምስጋና ከሕዝቦች ሁሉ ዘንድ እንዲፈልቁ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ቡቃያ እንደምታበቅል፣ የተክል ቦታ ችግኝ እንደሚያፈላ፣ ጌታ እግዚአብሔርም በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ ጽድቅንና ምስጋናን ያበቅላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርም ቡቃያውን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ደስታን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤ ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤ የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።
እናንተ ከላይ ያላችሁ ሰማያት! ጽድቅን እንደ ዝናብ አውርዱ፤ ደመናም ያርከፍክፈው፤ ምድር ትከፈት፤ ደኅንነትም ያቈጥቊጥ፤ እኔ እግዚአብሔር የፈጠርኩት ስለ ሆነ ጽድቅም ከእርሱ ጋር ይብቀል።”
“ትእዛዞቼን በጥንቃቄ ሰምታችሁ ቢሆንማ ኖሮ፥ በረከታችሁ እንደማይደርቅ የወንዝ ውሃ፥ ጽድቃችሁም እንደ ባሕር ሞገድ በብዛት በመጣላችሁ ነበር!
እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።
የሚሰጣት ፍርድ እንደ ንጋት እስኪፈነጥቅና መዳንዋም እንደሚነድ ችቦ እስኪበራ ድረስ፥ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ከማሰብ አላርፍም።
በመልካም መሬት ላይ የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ሰምቶ በማስተዋል የሚቀበለውን ሰው ነው፤ እርሱ ፍሬ ያፈራል፤ አንዱ መቶ፥ አንዱ ሥልሳ፥ አንዱ ሠላሳ ፍሬ ይሰጣል።”
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።