ኢሳይያስ 45:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመረጥኳቸውን የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን እንድትረዳ፥ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የማዕርግ ስምም ሰጥቼሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣ አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ አገልጋዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቁልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አገልጋዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ ተቀበልሁህም፤ አንተ ግን አላወቅኸኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፥ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም። |
የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።
አዳኛችሁ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ የሚዘምት ሠራዊት እልካለሁ፤ የከተማዋን ቅጽር በሮች እሰባብራለሁ፤ የባቢሎናውያንም ፉከራ ወደ ለቅሶ ይለወጣል።
ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”
በከተማችሁ እየተዘዋወርኩ የአምልኮ ስፍራዎቻችሁን ስመለከት ‘ለማይታወቅ አምላክ’ ተብሎ የተጻፈበትን የመሠዊያ ቦታ አገኘሁ፤ እንግዲህ እኔ አሁን የምነግራችሁ ስለዚሁ ሳታውቁ ስለምታመልኩት አምላክ ነው።
እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።