ሕዝቡ ግን ተዘርፈውና ተበዝብዘው በዋሻ ውስጥ ተዘግቶባቸዋል፤ በወህኒ ቤትም ተሸሽገዋል። ተዘረፉ፤ ተበዘበዙ፤ ማንም በመታደግ ሊያድናቸው አልቻለም።
ኢሳይያስ 42:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ መካከል ለዚህ ትኲረት ሰጥቶ ስለሚመጣው ጊዜ በጥንቃቄ የሚያዳምጥ ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚሰማ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው? |
ሕዝቡ ግን ተዘርፈውና ተበዝብዘው በዋሻ ውስጥ ተዘግቶባቸዋል፤ በወህኒ ቤትም ተሸሽገዋል። ተዘረፉ፤ ተበዘበዙ፤ ማንም በመታደግ ሊያድናቸው አልቻለም።
የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለዘራፊና ለቀማኛ አሳልፎ የሰጠ ማነው? ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ አይደለምን? ይህም የሆነው እኛ ስለ በደልነው፥ በሚፈቅደው መንገድ ስላልሄድንና ለሕጉም ታዛዦች ስላልሆንን ነው።
“ትእዛዞቼን በጥንቃቄ ሰምታችሁ ቢሆንማ ኖሮ፥ በረከታችሁ እንደማይደርቅ የወንዝ ውሃ፥ ጽድቃችሁም እንደ ባሕር ሞገድ በብዛት በመጣላችሁ ነበር!
አንቺ በደለኛ መሆንሽንና በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅሽን ብቻ እመኚ፤ ከባዕዳን አማልክት ጋር በየለምለሙ ዛፍ ሥር የጣዖት አምልኮ ርኲሰት መፈጸምሽንና ለሕጌም ያለመታዘዝሽን ተናዘዢ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?”