ኢሳይያስ 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና ታዳጊ የሆኑና በዕድሜ ያልጠኑ ልጆችንም መሪዎች አድርጎ ይሾምባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱ ላይ አለቆቻቸው እንዲሆኑ ጐልማሶችን እሾምባቸዋለሁ፤ ዘባቾችም ይገዙአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቻቸው እንዲሆኑ ብላቴኖችን አስነሣባቸዋለሁ፥ ሕፃናቶችም ይገዙአቸዋል። |
ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ አምላኩን እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ኢኮንያን በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ከዐሥር ቀን ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ገንዘብ አበዳሪዎች ሕዝቤን ያራቊታሉ፤ አራጣ አበዳሪዎችም ይበዘብዙአቸዋል፤ ሕዝቤ ሆይ፥ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጣምማሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ኲራት አብዝተዋል፤ አንገታቸውን አስረዝመው በዐይናቸው ይጠቅሳሉ፤ አረማመዳቸውን ለውጠው የእግራቸውን አልቦ እያቃጨሉ በቀስታ ይራመዳሉ።