ኢሳይያስ 23:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መርከበኞች ያበለጸጉአችሁ እናንተ የደሴቲቱ ሕዝብና የሲዶን ነጋዴዎች በሐዘን ጸጥ በሉ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፥ በባሕርም የሚሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች የሞሉባችሁ፥ ጸጥ በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደሴት የሚኖሩ በባሕር የሚሻገሩ የፊኒቄ ስደተኞች ምን ይመስላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በደሴት የምትኖሩ በባህርም የሚሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች ንግድ የሞሉባችሁ ሆይ፥ ጸጥ በሉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በደሴቶች የምትኖሩ ሕዝቦች! ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! ሕዝቦች ኀይላቸውን ያድሱ፤ ወደ ፊትም ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድ ሸንጎ በአንድነት እንገናኝ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤
“የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።