ኢሳይያስ 22:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አንተን ከደረጃህ ዝቅ ያደርግሃል፤ ከሥራህም ያባርርሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከኀላፊነትህም ትባረራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከሹመትህም ትሻራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአዛዥነት ሥራህና ከሥልጣንህ ትሻራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአዛዥነት ሥራ አሳድድሃለሁ፥ ከሹመትህም ትሻራለህ። |
በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”