ኢሳይያስ 19:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ ያለው አትክልት ሁሉ ይደርቃል፤ በወንዙ አጠገብ የተዘራውም ሰብል ሁሉ ደርቆ ነፋስ ይወስደዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በአባይ ዳር፣ በወንዙ መፋሰሻ ላይ ያሉት ተክሎች ይጠወልጋሉ። በአባይ ዳር የተዘራው ዕርሻ ሁሉ፣ በነፋስ ይወሰዳል፤ ምንም አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ፥ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፤ ይበተናል፤ ምንም አይቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ፥ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ በነፋስ ይመታል፤ ይደርቃልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም። |