ኢሳይያስ 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓባይ ውስጥ ያለው ውሃ ዝቅ ይላል፤ ወንዙም ቀስ በቀስ ይደርቃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአባይ ወንዝ ይቀንሳል፤ ውሃውም እየጐደለ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዐባይ ወንዝ ይጎድላል፤ ወንዙም እያነሰም ይሄዳል ደረቅም ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያን ከባሕር ውኃን ይጠጣሉ፤ ወንዙም ያንሳል፤ ደረቅም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። |
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ።
የዓባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ግብጽም በክፉ ሰዎች ሥልጣን ሥር እንድትወድቅ አደርጋለሁ። ስለዚህም ባዕዳን ሕዝብ አገሪቱን በሞላ ያጠፋሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች።
ግብጻውያንም በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ባይፈልጉ፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተን የዳስ በዓል አናከብርም” በሚሉ መንግሥታት ላይ የሚደርሰው ቀሣፊ በሽታ ይመጣባቸዋል።