በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
ኢሳይያስ 10:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የሠራዊት አምላክ በዖሬብ አለት አጠገብ በምድያማውያን ላይ እንዳደረግሁት አሦራውያንን የምቀጣበት ጅራፍ ባሕሩን በበትሬ መትቼ ግብጻውያንን እንደቀጣሁ አሦራውያንን እቀጣለሁ። በግብጽ ላይ በትሬን እንዳነሣሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይም አነሣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፣ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፣ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ምድያምን በመከራው ቦታ እንደ መታው ጅራፍን ያነሣበታል፤ ቍጣውም በባሕሩ መንገድና በግብፅ መንገድ በኩል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ምድያምን በሔሬብ ዓለት በኩል እንደ መታው ጅራፍ ያነሣበታል፥ በትሩም በባሕር ላይ ይሆናል፥ በግብፅም እንዳደረገ ያነሣዋል። |
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በጽዮን ለሚኖሩ ሕዝቦቹ እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ ከዚያ በፊት ግብጻውያን ጨቊነው እንደ ገዙአችሁ እነርሱም የጨቈኑአችሁ ቢሆንም አሦራውያንን አትፍሩ።
እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ በወጡ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ከአሦር የሚወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላቸዋል።
እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።
አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አበዛህ፤ በደስታም እንዲሞሉ አደረግሃቸው፤ ሰዎች መከር በሚሰበስቡበት፥ ወይም ምርኮ በሚካፈሉበት ጊዜ ደስ እንደሚላቸው ሕዝብህም አንተ ባደረግኸው ነገር ደስ ይላቸዋል።
በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤
ዖሬብና ዘኤብ የተባሉ ሁለት የምድያማውያን መሪዎችንም ማረኩ፤ ዖሬብን “የዖሬብ አለት” ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ፥ ዘኤብንም “የዘኤብ የወይን መጭመቂያ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ገደሉአቸው፤ ከዚህም በኋላ የቀሩትን ምድያማውያን ማሳደድ ቀጠሉ፤ የዖሬብንና የዘኤብንም ራሶች ቈርጠው ወደ ጌዴዎን አመጡለት፤ በዚያን ጊዜ ጌዴዎን ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ነበረ።