የቀድሞ አባቶቼና እኔ በሌሎች ሕዝቦች ላይ ምን እንዳደረግን አታውቁምን? ከሌሎች ሕዝቦች አማልእክት መካከል ሕዝቡን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያዳነ አምላክ አንድ እንኳ ይገኛልን?
ኢሳይያስ 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዓለም መንግሥታት ሁሉ በእኔ ፊት እንደ ወፍ ጎጆች ነበሩ፤ እንቊላል በቀላሉ እንደሚሰበሰብ ዐይነት ሀብታቸውን ሁሉ ሰብስቤ ወሰድኩ፤ ይህን ባደረግሁ ጊዜ የወፍ ላባ ያኽል እንኳ የተንቀሳቀሰ የለም፤ የወፍ ኩምቢ ያኽል እንኳ ድምፁን ያሰማ የለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ። በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፤ እንደ ተተወ እንቍላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጄም የአሕዛብን ኃይል እንደ ወፍ ቤት አገኘች፥ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፥ ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም። |
የቀድሞ አባቶቼና እኔ በሌሎች ሕዝቦች ላይ ምን እንዳደረግን አታውቁምን? ከሌሎች ሕዝቦች አማልእክት መካከል ሕዝቡን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያዳነ አምላክ አንድ እንኳ ይገኛልን?
በአገሪቱ ላይ መኖር የሚገባችሁ እናንተ ብቻ መስሎአችሁ፥ ቀድሞ በነበራችሁ ይዞታ ላይ ለመቀላቀል ሰዎችን ሁሉ እያስወጣችሁ ቤትን ከቤት ማያያዝና እርሻንም በእርሻ ላይ ለመቀላቀል ለምትፈልጉ ወዮላችሁ!
አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”
ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥ መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”