ሆሴዕ 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በጊብዓ ኃጢአት ከሠሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ከማሳዘን አልተቈጠቡም፤ ስለዚህ በገባዖን ጦርነት ይነሣባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤ በዚያም ጸናችሁ፤ በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ ጦርነት አልጨረሳቸውምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል ሆይ! ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፤ በዚያ ጸንተዋል፤ በዓመፀኛ ልጆች ላይ በጊብዓ ጦርነት አይደርስባቸውምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢአትን ሠርቶአል፤ በዚያም ጸንተዋል፤ በጊብዓ ላይ ጦር አይደርስባቸውምን? መጥቶም የዐመፅ ልጆችን ገሠጻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ሆይ፥ ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፥ በዚያ ጸንተዋል፥ በጊብዓ ላይ ሰልፍ አይደርስባቸውምን? |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
የእስራኤል ሕዝብ አዌን በተባለ ከተማ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት የሚሠሩባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ በመሠዊያዎቻቸውም ላይ እሾኽና አሜከላ ይበቅሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ተራራዎችን “ደብቁን!” ኮረብቶችንም “ጋርዱን!” ይላሉ።
ለጦርነት እንዲወጡ በገባዖን የመለከት፥ በራማም የጥሩንባ ድምፅ አሰሙ! በቤትአዌን “የብንያም ነገድ ሆይ! ከአንተ ጋር ነን” እያላችሁ ጩኹ!
የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ አደጋ ለመጣል መጥተው በሌሊት ቤቱን ከበቡት፤ በመጀመሪያ እኔን ለመግደል አስበው ነበር፤ በኋላ ግን በቊባቴ ላይ ተረባርበው ስላመነዘሩባት ሞተች፤