ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።
ዕብራውያን 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ የተነገረለት ካህን ከሌላ ነገድ ነው፤ ከዚህ ነገድ ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ የተነገረለት እርሱ ከሌላ ነገድ ነው፤ ከዚያም ነገድ በመሠዊያ ያገለገለ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ነገር የተነገረለት እርሱ ከሌላ ነገድ ነው፤ ከዚያም ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ነገር የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን ተካፍሎአልና፥ ከዚያም መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ነገር የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን ተካፍሎአልና፥ ከዚያም መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም፤ |
ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።
ከዚያም በኋላ እኔ ለክህነት የምመርጠው ሰው በትሩ በማቈጥቈጥ ትለመልማለች፤ በዚህም ዐይነት እነዚህ እስራኤላውያን በየጊዜው በአንተ ላይ ማጒረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ።”
እንግዲህ ለሕዝቡ ሕግ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ነው፤ በዚህ በሌዋውያን ክህነት ፍጹምነት ቢገኝ ኖሮ የአሮን የክህነት ሹመት ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣት ባላስፈለገም ነበር፤