በዚያን ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ማንኛውም ምክር ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፤ ቀድሞ ዳዊት አሁን ደግሞ አቤሴሎም የእርሱን ምክር ይከተሉ ነበር።
ዕብራውያን 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፣ ገና የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያ ትምህርት የሚያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋል፤ የሚያስፈልጋችሁም ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ አሁን በነበረው ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ እንደገና የእግዚአብሔር ቃላት የመጀመሪያውን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መምህራን ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ ካመናችሁ ጀምሮ በትምህርት ላይ የቈያችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእግዚአብሔርን የቃሉን መጀመሪያ ትምህርት ሊያስተምሩአችሁ ትወዳላችሁ፤ ወተትንም ሊግቱአችሁ ትሻላችሁ፤ ጽኑ ምግብንም አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። |
በዚያን ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ማንኛውም ምክር ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፤ ቀድሞ ዳዊት አሁን ደግሞ አቤሴሎም የእርሱን ምክር ይከተሉ ነበር።
ዕዝራ መላ ሕይወቱን የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናትና በተግባር በመተርጐም፥ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች፥ ሕጎችና ሥርዓቶች ለመላው የእስራኤል ሕዝብ በማስተማር ያውለው ነበር።
እግዚአብሔር ፊደል በፊደል ላይ፥ መስመር በመስመር ላይ፥ ትምህርት በትምህርት ላይ እያነባበረ ሊያስተምራችሁ የፈቀደው ስለዚህ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርምጃችሁ ሁሉ ትሰናከላላችሁ፤ ትቈስላላችሁ፤ በወጥመድም ተይዛችሁ ትታሰራላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውሃው ኑ! የምትገዙበት ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ! ኑና ያለ ገንዘብና ያለ ዋጋ ወተትና የወይን ጠጅን ግዙ።
ኢየሱስም “እናንተ የማታምኑ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታምኑ ሰዎች! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!”
በበረሓ ተሰብስቦ ከነበረው ሕዝብ ጋርና ከሲና ተራራ ላይ ከተናገረው መልአክ ጋር እንዲሁም ከአባቶቻችን ጋር የነበረው እርሱ ነው። የእግዚአብሔርን የሕይወት ቃል ለእኛ ያስተላለፈልንም ይኸው ሙሴ ነው።
ነገር ግን በተለያዩ ቋንቋዎች በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ቃሎችን ከምናገር ይልቅ ሌሎችን ለማስተማር ስል በቤተ ክርስቲያን አምስት ቃላትን በሚታወቅ ቋንቋ በአእምሮዬ መናገር እወዳለሁ።
በመጨረሻም ወንድሞቼ ሆይ! በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ያንን ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ነገር ደግሜ ብጽፍላችሁ እኔን አያሰለቸኝም፤ እናንተን ግን ከስሕተት ሊጠብቃችሁ ይችላል።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
እንግዲህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ፍጹም ወደህ ኦነው ትምህርት እንለፍ፤ ከሞተ ሥራ ንስሓ የመግባትንና በእግዚአብሔር የማመንን መሠረት እንደገና አንመሥርት፤
የሚያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያስተምር ያስተምር፤ የሚያገለግልም እግዚአብሔር በሚሰጠው ኀይል ያገልግል፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሁሉ ነገር ይመሰገናል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።