ዕብራውያን 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ፍላጎት መላእክትን ሳይሆን የአብርሃምን ዘር ለመርዳት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የመጣው መላእክትን ለመርዳት ሳይሆን፣ የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንደ ሆነ ግልጽ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንጂ ትኩረቱ ለመላእክት አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነሣውን ከአብርሃም ዘር እንጂ ከመላእክት የነሣው አይደለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። |
እግዚአብሔርም ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋ ቃል የሰጠው በዚህ ዐይነት ነው፤ መጽሐፍ የተስፋ ቃል ከአብርሃም በኋላ የተሰጠው ለብዙዎች እንደ ሆነ አድርጎ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደ ሆነ አድርጎ “ለዘርህ” ይላል፤ ይህም “ዘርህ” የተባለው ክርስቶስ ነው።
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።