ዕብራውያን 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በቅዱሳት መጻሕፍት “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ” ይላል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ይላል፤ “ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በማለት፥ “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስምህን ለወንድሞች እነግራቸዋለሁ፤ በማኅበር መካከልም አመሰግንሃለሁ” አለ። |
ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለሰው ሁሉ በግልጥ ተናገርኩ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኲራብም ሆነ በቤተ መቅደስ፥ ዘወትር አስተማርኩ፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም፤
ስማቸው በሰማይ ወደተጻፈው፥ የቤተ ክርስቲያን የበኲር ልጆች ወደሆኑት ወደ አማኞች ጉባኤ፥ የሁሉ ፈራጅ ወደ ሆነው አምላክና ፍጹምነትን ወዳገኙት የጻድቃን ነፍሳት ቀርባችኋል።