ዕንባቆም 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግንቡ ድንጋዮች ከግድግዳው ይጮኻሉ፤ የእንጨት ምሰሶችም ይህንኑ ከውስጥ ያስተጋባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋይ ከቅጥሩ ውስጥ ይጮኻል፤ ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይመልሱለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋይ ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከወራጅ ይመልስለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል። |
በኢየሩሳሌም ቅጥር ውስጥ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር ጩኹ! ዕንባችሁም ሌሊትና ቀን እንደ ጐርፍ ይውረድ፤ በፍጹም ዕረፍት አታድርጉ፤ ለዐይኖቻችሁም ፋታን አትስጡ።
ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የነገረንን ቃል ሁሉ ስለ ሰማ ይህ ድንጋይ በእኛ ላይ ምስክር ነው፤ ስለዚህም አምላካችሁን ብትክዱ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችኋል።”
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።