Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕንባቆም 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሰውን በመግደል ከተማን ለምትቈረቊሩና፥ በበደል ዋና ከተማን ለምትሠሩ ወዮላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚሠራ፣ በወንጀልም ለሚመሠርታት ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በበደል ለሚመሠርት ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar




ዕንባቆም 2:12
12 Referencias Cruzadas  

በአክዓብ ዘመነ መንግሥት ሒኤል ተብሎ የሚጠራ የቤትኤል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ሒኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ የበኲር ልጁ አቢራም ሞተበት፤ የቅጽርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ ወዮላት! ማገዶውን እኔ ራሴ አብዝቼ እጨምራለሁ።


እናንተ ደም በማፍሰስ ጽዮንን፥ በደል በመሥራት ኢየሩሳሌምን የምትገነቡ ናችሁ።


ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ፥ ፈጽማ አታላይ ለሆነች፥ በዝርፊያ ለታወቀችና በብዙ ምርኮ ለተሞላች ለነነዌ ከተማ ወዮላት!


ሰው ሁሉ እንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ በመሳለቂያ እንቆቅልሽ እንዲህ ይላል፦ “ያንተ ያልሆነውን የምታግበሰብስ ወዮልህ! በመያዣነት በተወሰዱ ዕቃ ራስህን የምታበለጽገው እስከ መቼ ነው?”


እኛን ከእናንተ ጋር በክርስቶስ እንድንጸና ያደረገን እግዚአብሔር ነው፤ ለሥራ የለየንም እርሱ ነው፤


በዚያን ጊዜ ኢያሱ፦ “ይህቺን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሣ የተረገመ ይሁን፤ መሠረቱን ሲጥል የበኲር ልጁ ይጥፋ፤ መዝጊያውን ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ፤” ብሎ ረገመ።


ያቺ ሴት በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየኋት፤ ባየኋትም ጊዜ እጅግ በጣም ተደነቅሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos