ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ዘፍጥረት 50:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖንም ይህን ሰምቶ “ቃል በገባህለት መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “በአስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “ሂድ፥ አባትህን እንዳስማለህ ቅበረው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “ውጣ፤ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ ውጣ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው አለው። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ እዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው።
ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፤ የፈርዖን ባለሥልጣኖችና በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ ታላላቅ ሰዎች፥ ሌሎችም የግብጽ መኳንንት ዮሴፍን ተከትለው ሄዱ።