ዘፍጥረት 49:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤ በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአሴር እንጀራ ወፍራም ነው፤ እርሱም ለአለቆች ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይስጣል። |