ዘፍጥረት 49:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዳን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ለሆነው ሕዝብ ፈራጅ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዳን ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ በወገኑ ይፈርዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳም በወገኑ ይፈርዳል ከእስርኤል ነገስ እንደ አንዱ |
ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።
በዚያን ዘመን ጾርዓ በምትባል ከተማ የሚኖር ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከዳን ነገድ ነበር፤ ሚስቱ መኻን ስለ ነበረች ልጆች አልወለደችም፤