እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 49:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤ ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤ የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤ የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል፥ እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል፥ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛብሎን ጫማውን አዝቦ ይኖራል፤ እርሱም እንደ መርከቦች ወደብ ይሆናል፤ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ይሰፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል ዳርቻውም እስከ ሲዶን ድረስ ነው። |
እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።