እነርሱም ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸውና በአህዮቻቸው፥ በበጎቻቸውና በፍየሎቻቸው በከብቶቻቸውም ለውጥ እህል ሰጣቸው፤ ያንንም ዓመት በሙሉ በከብቶቻቸው ልዋጭ እህል ሰጣቸው።
ዘፍጥረት 47:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚቀጥለውም ዓመት ወደ እርሱ መጡና እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ! ከአንተ የምንሰውረው ነገር የለም፤ ገንዘባችን ሁሉ አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም ለአንተ አስረክበናል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ዓመት ካለፈ በኋላ ሕዝቡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዮሴፍ መጥተው እንዲህ አሉት፣ “እንግዲህ ከጌታችን የምንሰውረው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችን ዐልቋል፤ ከብቶቻችንንም አስረክበንሃል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው፣ ከመሬታችንና ከእኛ ከራሳችን በቀር አንዳች ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመቱም ተፈጸመ፥ በሁለተኛውም ዓመት ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ አሉት፦ “እኛ ከጌታችን አንሰውርም፥ ብሩ በፍጹም አለቀ፥ ከብታችንም ከጌታችን ጋር ነው፥ ከሰውነታችንና ከምድራችን በቀር በጌታችን ፊት አንዳች የቀረ የለም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያችም ዓመት ተፈጸመች፤ በሁለተኛዋም ዓመት ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ አሉት፥ “እኛ ለጌታችን ሞተን እንዳናልቅበት እህል ስጠን፤ ብሩ በፍጹም አለቀ፤ ንብረታችንና ከብታችንም በጌታችን ዘንድ ነው፤ ከሰውነታችንና ከምድራችን በቀር በጌታችን ፊት አንዳች የቀረን የለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመቱም ተፈጸመ በሁለተኛውም ዓመት ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ አሉት፦ እኛ ከጌታችን አንሰውርም ብሩ በፍጹም አለቀ ከብታችንም ከጌታችን ጋር ነው ከሰውነታችንና ከምድራችን በቀር በጌታችን ፊት አንዳች የቀረ የለም እኛ በፈትህ ስለ ምን እንሞታለን? |
እነርሱም ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸውና በአህዮቻቸው፥ በበጎቻቸውና በፍየሎቻቸው በከብቶቻቸውም ለውጥ እህል ሰጣቸው፤ ያንንም ዓመት በሙሉ በከብቶቻቸው ልዋጭ እህል ሰጣቸው።
እኛና ምድራችን በፊትህ እንጥፋን? እኛንና መሬታችንን ገዝተህ እህል ስጠን፤ እኛ የንጉሡ ባሪያዎች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፤ በልተን በሕይወት እንድንኖር እህል ስጠን፤ በመሬታችን ላይ የምንዘራውም ዘር ስጠን።”
አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ በከተማይቱ የቅጽር ግንብ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ንጉሥ ሆይ፥ እባክህ እርዳኝ!” ስትል ጮኸች።
“ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”