La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 45:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለአባቱም በዐሥር አህዮች የተጫነ ከግብጽ ምድር የሚገኘውን መልካም ነገር ሁሉ ላከለት፤ እንዲሁም በሚመጣበት ጊዜ ለስንቅ የሚሆነው በሌሎች ዐሥር እንስት አህዮች የተጫነ እህል፥ ዳቦና ሌላም ምግብ ላከለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለአባቱም በግብጽ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም ለመንገዱ ስንቅ የሚሆነው እህል፣ ዳቦና ሌላ ምግብ በዐሥር እንስት አህዮች አስጭኖ ሰደደለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለአባቱም እንደዚሁ፥ በዐሥር አህዮች የተጫነ ከግብጽ ምድር የሚገኘውን መልካም ነገር ላከለት፤ እንዲሁም በሚመጣበት ጊዜ ለስንቅ የሚሆነው በሌሎች ዐሥር እንስት አህዮች የተጫነ እህል፥ ዳቦና ምግብ ላከለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ባ​ቱም እን​ደ​ዚሁ ላከ፤ ከግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ የተ​ጫኑ ዐሥር አህ​ዮ​ችን፥ ደግ​ሞም በመ​ን​ገድ ለአ​ባቱ ስንቅ የተ​ጫኑ ዐሥር በቅ​ሎ​ዎ​ችን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአባቱም እንደዚሁ ሰደደ የግብፅ በረከት የተሸከሙ አሥር አህዮችን ደግሞም በመንገድ ለአባቱ ስንቅ ስንዴና እንጀራ የተሸከሙ አሥር ሴቶች አህዮችን።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 45:23
5 Referencias Cruzadas  

የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዐሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።


አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።


ለእያንዳንዳቸውም አንድ አንድ የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን አምስት የክት ልብስና ሦስት መቶ ብር ሰጠው።


በዚህ ሁኔታ ወንድሞቹን ካሰናበታቸው በኋላ “በመንገድ አትጣሉ” ብሎ መከራቸው።


“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”