እንግዲህ ታማኝነታችሁ ተፈትኖ የሚረጋገጠው በዚህ ነው፤ ታናሽ ወንድማችሁ እስከሚመጣ ድረስ እንደማልለቃችሁ በንጉሡ በፈርዖን ስም እምላለሁ።
ዘፍጥረት 42:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት የተናገራችሁት ሁሉ እውነት መሆኑ ይረጋገጣል፤ ከመሞትም ትድናላችሁ።” እነርሱም በዚህ ነገር ተስማሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ ነገራችሁም የታመነ ይሆናልና አትሞቱም። |
እንግዲህ ታማኝነታችሁ ተፈትኖ የሚረጋገጠው በዚህ ነው፤ ታናሽ ወንድማችሁ እስከሚመጣ ድረስ እንደማልለቃችሁ በንጉሡ በፈርዖን ስም እምላለሁ።
ሰውየውም እንዲህ አለን፤ ‘ታማኞች ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው ይህን አንድ ነገር ብታደርጉ ነው፤ ይኸውም ከእናንተ አንዱ ከእኔ ጋር ይቈይ፤ ሌሎቻችሁ ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ ወደ አገራችሁ ተመለሱ፤
ታናሽ ወንድማችሁንም ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት ታማኞች ሰዎች መሆናችሁንና ሰላዮችም አለመሆናችሁን አረጋግጣለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ በዚህም አገር ቈይታችሁ እንደ ፈለጋችሁ መነገድ ትችላላችሁ።’ ”
ጌታችንም ለአንተ ለጌታችን ነግረንህ አገልጋዮቹን ‘ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ በፊቴ አትቀርቡም’ ብለህ በብርቱ አስጠነቀቅከን።