ዘፍጥረት 41:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፦ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን? |
“አንተም ዕዝራ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብና ዕውቀት እየተመራህ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ሕግ የሚመሩትን፥ በኤፍራጥስ ማዶ የሚገኙትን ሰዎች የሚመሩ አስተዳዳሪዎችንና ዳኞችን ሹምላቸው፤ ለማያውቁትም ሁሉ የአምላክህን ሕግ አስተምራቸው፤
በጾዓን ያሉ የንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ጠቢባን የሆኑት የግብጽ ንጉሥ አማካሪዎች ጥቅም የሌለው ምክር ይመክራሉ፤ እንዴት አድርገው ለንጉሡ “እኛ ብልኆች ነን፤ ዘራችንም ከቀድሞ ነገሥታት ሲወርድ፥ ሲዋረድ የመጣ ነው” ይላሉ?
“እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።”
የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በመንግሥትህ አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመነ መንግሥት እንደ አማልክት የሆነ ዕውቀት፥ ጥበብና ማስተዋል የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ በዚህም ምክንያት አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆር የጠንቋዮች፥ የአስማተኞች፥ የጠቢባንና የኮከብ ቈጣሪዎች ሁሉ አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር።
ዳንኤል ባለው ልዩ የሥራ ችሎታ ከሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በልጦ መገኘቱን በተግባር አስመሰከረ፤ ስለዚህ ንጉሡ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሊሾመው አሰበ።
ከዚህ በኋላ ሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በዳንኤልና በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ ላይ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ወንጀል ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል እጅግ ጠንቃቃና ታማኝ ስለ ነበር ምንም ዐይነት ስሕተት ወይም በደል ሊያገኙበት አልቻሉም።