የእንጀራ ቤት ኀላፊውም ዮሴፍ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ሕልም የሰጠው ትርጒም መልካም መሆኑን ባየ ጊዜ፥ የእርሱንም ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ “እኔም በበኩሌ ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ ‘ሦስት መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤
ዘፍጥረት 40:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁሉ በላይ ባለው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ ልዩ ልዩ ምግብ ነበረበት፤ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሡ ይበሉት ነበር።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይኛውም መሶብ ፈርዖን የሚበላው ጋጋሪው በያይነቱ የሠራው መብል ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይኛውም መሶብ ፈርዖን ከሚበላው ከጋጋዎች ሥራ ሁሉ ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር። |
የእንጀራ ቤት ኀላፊውም ዮሴፍ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ሕልም የሰጠው ትርጒም መልካም መሆኑን ባየ ጊዜ፥ የእርሱንም ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ “እኔም በበኩሌ ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ ‘ሦስት መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤
ከምናሴ ነገድ ዳዊት በተመለሰ ጊዜ ወደ እርሱ የሄዱት ወታደሮች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ ዓድናሕ፥ ዮዛባድ፥ ይዲዕኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባድ፥ ኤሊሁና ጺለታይ፤ እነዚህ ሁሉ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሺህ አለቅነት ማዕርግ የነበራቸው ናቸው።