ዘፍጥረት 39:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ዘላቂ ፍቅሩን አሳየው፤ በእስር ቤቱ አዛዥ ዘንድ ባለሟልነትን እንዲያገኝ አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፤ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፤ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት |
እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ አደረገ፤ በእርግጥም የንጉሡ ባለሟሎችና ሕዝቡ ሁሉ ሙሴን በግብጽ ምድር ታላቅ ሰው አድርገው ተመለከቱት።
እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙና የጠየቁትንም ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን የግብጽን ሀብት በዝብዘው ሄዱ።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”