ዘፍጥረት 38:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦናን የሚወለዱት ልጆች የእርሱ ያለመሆናቸውን በማወቁ ወደ ወንድሙ ሚስት ሲገባ ዘሩን ወደ ምድር ያፈሰው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በወንድሙ ስም ልጆች እንዳይወለዱ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፥ ከወንድሙ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን ዐወቀ፤ ወደ ወንድሙ ሚስትም በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይተካ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይስጥ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። |
“ወንድማማቾች በአንድ ርስት ላይ ቢኖሩና አንደኛው ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰብ ውጪ የሆነ ሌላ ሰው ማግባት አይኖርባትም፤ የባልዋ ወንድም እርስዋን በማግባት የዋርሳነት ግዴታውን ይፈጽምላት።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ በመጀመሪያ የሚወለደው ወንድ ልጅ በሟቹ ስም ይጠራ፤ በዚህም ዐይነት በእስራኤል የሟቹ የትውልድ ሐረግ ሳይጠፋ መቀጠል ይችላል።
እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።
ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን?
በተጨማሪም የሟቹ የማሕሎን ሚስት ሞአባዊቷ ሩት ሚስቴ ትሆናለች፤ ይህም ንብረቱ ከሟቹ ቤተሰብ እንዳይወጣና የትውልድ ሐረጉም ከወንድሞቹ መካከልና ከሀገሩ አደባባይ እንዳይጠፉ ያደርገዋል፤ ለዚህ ሁሉ ዛሬ እናንተ ምስክሮች ናችሁ።”