Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 25:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ወንድማማቾች በአንድ ርስት ላይ ቢኖሩና አንደኛው ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰብ ውጪ የሆነ ሌላ ሰው ማግባት አይኖርባትም፤ የባልዋ ወንድም እርስዋን በማግባት የዋርሳነት ግዴታውን ይፈጽምላት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች በአ​ን​ድ​ነት ቢቀ​መጡ፥ አን​ዱም ልጅ ሳይ​ኖ​ረው ቢሞት፥ የሞ​ተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አት​ሂድ፤ ነገር ግን የባ​ልዋ ወን​ድም ወደ እር​ስዋ ገብቶ እር​ስ​ዋን ያግባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይኑር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 25:5
11 Referencias Cruzadas  

አንድ ቀን ታላቂቱ ልጁ እኅትዋን እንዲህ አለቻት፦ “አባታችን ማርጀቱ ነው፤ ልጆች እንድንወልድ እኛን የሚያገቡ ወንዶች በዙሪያችን የሉም፤


“መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ የሟቹን ሚስት አግብቶ ለሟቹ ዘር ይተካለት፤’ ብሎአል።


“መምህር ሆይ፥ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሴትዮዋን አግብቶ ለሟቹ ዘር ይተካለት፤’ ብሎ ሙሴ ጽፎልናል።


“መምህር ሆይ! ሙሴ እንዲህ ሲል ጽፎልናል፤ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሴትዮዋን አግብቶ ለሟቹ ዘር ያትርፍለት።’


ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን?


እስኪነጋ እዚሁ ቈዪ! ሲነጋም ያ ሰው ስለ አንቺ ኀላፊነትን የሚወስድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እጠይቀዋለሁ፤ እርሱ ኀላፊነትን የሚወስድ ከሆነ መልካም ነው፤ የማይወስድ ከሆነ ግን ስለ አንቺ ኀላፊነትን እኔ እንደምወስድ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አሁንም ተኚ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ቈዪ።”


ስትቃርሚ አብረውሽ የነበሩት ሴቶች የሚያገለግሉት ቦዔዝ የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እነሆ! እርሱ ዛሬ ማታ ገብስ ይወቃል፤


“አንቺ ማን ነሽ?” ብሎም ጠየቃት። እርስዋም “ጌታዬ ሆይ! አገልጋይህ እኔ ሩት ነኝ፤ አንተ የቅርብ ዘመድ ስለ ሆንክ ለእኔ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት አለብህ፤ ስለዚህ ልብስህን ባገልጋይህ ላይ ጣል አለችው።”


ቦዔዝም “መሬቱን ከናዖሚ የምትገዛ ከሆነ በውርሱ የሟቹን ስም ታስጠራ ዘንድ ባልዋ የሞተባትን ሞአባዊትዋን ሩትንም አብረህ ትወስዳለህ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos